Get Mystery Box with random crypto!

ስማርት ስልክን ለአንድ ወር ባለመጠቀም ብቻ 10 ሺህ ዶላር የሚያሸልመው ውድድር! የአሜሪካው ታ | Big Habesha

ስማርት ስልክን ለአንድ ወር ባለመጠቀም ብቻ 10 ሺህ ዶላር የሚያሸልመው ውድድር!

የአሜሪካው ታዋቂ እርጎ አቅራቢ ኩባንያ “ሲጂ ዲያሪ” በዲጂታሉ አለም የሚደርስ መረበሽን የሚያስቀር ውድድር ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

ከ311 ሚሊየን በላይ ሰዎች ስማርት ስልክ ተጠቃሚ ባለባት አሜሪካ እያንዳንዱ ሰው በቀን በአማካይ 5 ስአት ከ25 ደቂቃዎችን ስማርት ስልኩ ላይ እንደሚያጠፋ ጥናቶች ያመለክታሉ። ይህም ማህበራዊ መስተጋብርን እያጠፋ ለተለያዩ የጤና እክሎች እየዳረገ እንደሚገኝም ተደጋግሞ ይነሳል።

“ሲጂ ዲያሪ” ያዘጋጀው “ከዲጂታሉ አለም የመንጻት ውድድር”ም ለጉዳዩ ትኩረት ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል።

በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑት የ10 ሺህ ዶላር እና ሌሎች ሽልማቶች ይሰጣቸዋል መባሉንም ዩናይትድ ፕረስ ኢንተርናሽናል ዘግቧል። ሽልማቱ የሚያጓጓ ቢመስልም ከስማርት ስልክ ለወር አይደለም ለአንድ ቀን መራቅ የሚከብዳቸው በርካታ ናቸው።

“ብዙ መረበሽ የሌለበት ቀላል ህይወት መኖር ያለውን ፋይዳ በአግባቡ እንረዳለን፤ አሁን ላይ ኑሯችን እየረበሹ ከሚገኙ ጉዳዮች ስልኮቻችን ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ” የሚለው ኩባንያው፥ ከዚህ ቀደምም ለአንድ ወር አልኮል ያለመጠጣት ውድድር ማካሄዱ ይታወሳል።

ለመሆኑ እርሶ ለ30 ቀናት ስልክዎን ከጎንዎ አርቀው 10 ሺህ ዶላር ይሸለማሉ ቢባሉስ ምን ይላሉ

ምንጭ-አልዐይን