Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ Quantum Computing ምንድነው? Quantum Computer: የQuantum M | Big Habesha

​​​ Quantum Computing ምንድነው?

Quantum Computer: የQuantum Mechanics ሀሳቦችን በመጠቀም አሁን ካሉት ኮምፒተሮች በፍጥነትና በተሻለ መልኩ ስራውን ሚከውን የኮምፒተር ዐይነት ነው!

አሁን ዓለም ላይ ያሉት ኮምፒተሮች በሙሉ ዳታዎችን ለማስቀመጥ ሆነ ለማስተላለፍ Binary Digit ተብሎ በሚጠራው የ 0 እና 1 ስብስብ የሆነው Streams of Bits (ባጭሩ Bits) ተጠቅመው ነው. .. ስእሎች, ቪድዮዎች, ሙዚቃዎች ብሎም ማንኛውም ኮምፒተሮች ላይ ያሉት ዶክመንቶች በBit መልኩ ነው ሚቀመጡት።

Bit እና Qubit ሚለያቸው፣ Bit ብለን የጠራናቸው ወይ 0 ወይ 1 በመሆን ነው ሚቀመጡት። Qubits ሚባሉት ግን እንደ Bits ለየብቻ 1 እና 0 መሆን ይችላሉ ደግሞም በተመሳሳይ ቦታና ግዜ 1ም 0ም ሆነው መቀመጥ ይችላሉ፥ ይህ Superposition ተብሎ ይጠራል። አሁን በምንጠቀማቸው ኮምፒተሮችና በQuantem Computers መሃል ያለው ትልቁ ልዩነትም ይሄኛው ነው።

አሁን በዋነኝነት የIBM ሪሰርቸሮችን ጨምሮ ብዙ ኩባንያዎች Quantum Computing ላይ ተስፋ ሰጪ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም፥ በሜዲካል፣ ኬሚስትሪና ኮምፒቲንጉ አለም ያበረክተዋል ተብሎ ከታሰበለት አላማ ብዙም እምርታ አላሳየም።