Get Mystery Box with random crypto!

የ 666 ሚስጥራት እና ሴራ ፡

Logo saluran telegram antiilluminati666 — የ 666 ሚስጥራት እና ሴራ ፡
Logo saluran telegram antiilluminati666 — የ 666 ሚስጥራት እና ሴራ ፡
Alamat saluran: @antiilluminati666
Kategori: Tidak terkategori
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 275
Deskripsi dari saluran

🌍አለማችን ሁሉ እንቅስቃሴዋ በኢሉሚናቲዎች ሴራ ነዉ: : _ የእያንዳዳችን እንቅስቃሴ በእነሱ እጅ ነዉ ስለዚህ በየቀኑ ነቅተን መከታተል እና ሴራቸዉን መቃወም !

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru

2023-03-02 14:31:13
ሼር!!!!!!!!!!
በቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦታ ላይ ጥይት፣ ጭስ እና ቦንብ !!!
ለታሪክ የሚቀመጥ ቪድዮ!
አድዋን ለማክበር በወጣው ኢትዮጵያዊ ህዝብ ላይ የአገር ሻጫ ባንዳ የጣልያን እንቁላል ቀቃይ የሆነው የምእራባውያን ተላላኪው የዘንዶው መንግስት ጥይት እና አስለቃሽ ጭስ በህጻናት እና በወጣቱ ላይ በመወርወር የጥቁሮች የነጻነት በአል የሆነውን አድዋን እንዳያከብሩ በማድረግ ታሪክ የማይረሳው ጠባሳ ዛሬ ጽፏል!!!!

እባካችሁ ቪድዮዎችን ሼር እናድርግ ድምጻችን ይሰማ!!
207 views11:31
Buka / Bagaimana
2023-02-09 08:04:35 ★ዓቢይ አህመድ ጸቡ ከክርስቶስ ጋር ነው።★

★ አንድ ሲኖዶስ ፣አንድ ፓትርያርክ የምንልበት ምክንያት ይሄ ነው።†

ከክርስቶስ የተገኘውና በቅዱሳን ሐዋርያት በኩል ወደ እኛ የመጣው ያልተቋረጠው የእስከንድርያው መንበረ ማርቆስ ስልጣነ ክህነት ቅብብሎሽ(apostolic succession)ይሄ ነው ።

ሼር በማድረግ ለሕዝብ አስተምሩ

ኢየሱስ ክርስቶስ

1. ማርቆስ
2. አንያኖስ
3. ሜልያስ
4. ክርዳኑ
5. አምብርዮስ
6. ዮስጦስ
7. አውማንዮስ
8. መርክያኖስ
9. ክላውያኖስ
10. አክርጵያኖስ
11. ዮልዮስ
12. ድሜጥሮስ
13. ያሮክላ (ሔራክልስ)
14. ዲዮናስዮስ
15. መክሲሞስ
16. ቴዎናስ
17. ጴጥሮስ (ተፍጻሜተ ሰማዕት)
18. አኪላስ
19. እለእስክንድሮስ
20. አትናቴዎስ
21. ጴጥሮስ 2ኛ
22. ጢሞቴዎስ
23. ቴዎፍሎስ
24. ቄርሎስ
25. ዲዮስቆሮስ
26. ጢሞቴዎስ 2ኛ
27. ጴጥሮስ 3ኛ
28. አትናቴዎስ 2ኛ
29. ዮሐንስ
30. ዮሐንስ 2ኛ
31. ዲዮስቆሮስ 2ኛ
32. ጢሞቴዎስ 3ኛ
33. ቴዎዶስዮስ (ቴውዳስስ)
34. ጴጥሮስ 4ኛ
35. ድምያኖስ
36. አንስጣስዮስ
37. አንድራኒቆስ
38. ብንያሚን
39. ያቃቱ (አጋቶን)
40. ዮሐንስ 3ኛ
41. ይስሐቅ
42. ስምዖን
43. እለእስክንድሮስ 2ኛ
44. ቆዝሞስ
45. ቴዎድሮስ
46. ካኤል (ሚካኤል)
47. ሚናስ
48. ዮሐንስ 4ኛ
49. ማርቆስ 2ኛ
50. ያዕቆብ 1ኛ
51. ስምዖን 2ኛ
52. ዮሳብ 1ኛ (ዮሴፍ)
53. ካኤል (ሚካኤል) 2ኛ
54. ቆዝሞስ 2ኛ
55. ስንትዮ 1ኛ
56. ሚካኤል 1ኛ
57. ገብርኤል 1ኛ
58. ቆዝሞስ 3ኛ
59. መቃርዮስ 1ኛ
60. ታውፋኔዎስ
61. ሚናስ 2ኛ
62. አብርሃም
63. ፊላታዎስ
64. ዘካርያስ
65. ስንትዩ 2ኛ
66. ክርስቶዶሉ (ገብረ ክርስቶስ)
67. ቄርሎስ 2ኛ (ጌርሎስ)
68. ሚካኤል 2ኛ
69. መቃርዮስ 2ኛ (መቃርስ)
70. ገብርኤል 2ኛ
71. ሚካኤል 3ኛ
72. ዮሐንስ 5ኛ
73. ማርቆስ 3ኛ
74. ዮሐንስ 6ኛ
75. ቄርሎስ 3ኛ
76. አትናቴዎስ 3ኛ
77. ገብርኤል 3ኛ
78. ዮሐንስ 7ኛ
79. ታውዳስዮስ 2ኛ
80. ዮሐንስ 8ኛ
81. ዮሐንስ 9ኛ
82. ብንያሚን 2ኛ
83. ጴጥሮስ 5ኛ
84. ማርቆስ 4ኛ
85. ዮሐንስ
86. ገብርኤል 4ኛ
87. ማቴዎስ 1ኛ
88. ዮሐንስ 5ኛ
89. ዮሐንስ 11ኛ
90. ማቴዎስ 2ኛ
91. ገብርኤል 6ኛ
92. ሚካኤል 4ኛ
93. ዮሐንስ 12ኛ
94. ዮሐንስ 13ኛ
95. ገብርኤል 7ኛ
96. ዮሐንስ 14ኛ
97. ገብርኤል 8ኛ
98. ማርቆስ 5ኛ
99. ዮሐንስ 15ኛ
100. ማቴዎስ 3ኛ
101. ማርቆስ 6ኛ
102. ማቴዎስ 4ኛ
103. ዮሐንስ 16ኛ
104. ጴጥሮስ 6ኛ
105. ዮሐንስ 17ኛ
106. ማርቆስ 7ኛ
107. ዮሐንስ 18ኛ
108. ማርቆስ 8ኛ
109. ጴጥሮስ 7ኛ
110. ቄርሎስ 4ኛ
111. ጴጥሮስ 8ኛ
112. ቄርሎስ 5ኛ
113. ዮሐንስ 19ኛ
114. መቃርዮስ 3ኝእ
115. ዮሳብ (ዮሴፍ) 2ኛ
116. ቄርሎስ 6ኛ
117. ባሲልዮስ
118. ቴዎፍሎስ
119. ተክለሃይማኖት
120. መርቆሬዎስ
121. ጳውሎስ
122. ማትያስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሐዋሪያዊት ናት የምንለው በምክንያት ነው ።
ሀዋሪያቶች በሰበሰቧት በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን !

#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_መንበር
#አንድ_ፓትሪያርክ
239 views05:04
Buka / Bagaimana
2023-02-09 08:04:13
166 views05:04
Buka / Bagaimana
2023-02-08 22:07:54
ዘንዶው ሰልፍ ከልክሏል!!!

ሰበር ዜና!!

መንግሥት ቤተ ክርስቲያን የጠራችው ሰልፍ እንዳይካሄድ ትዕዛዝ ሰጠ!!

ከፀጥታና ደኅነት የጋራ ግብረ–ኃይል ወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ የገመገመው የፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋራ ግብረኃይሉ በተለያዩ ሚዲያዎች ከሚሰራጩ ዘገባዎችና በመረጃ ስምሪቱ ባሰባሰባቸው ግብዓቶች መሠረት በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ
የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት አጋጣሚ እንዲፈጠር ቅስቀሳዎች እየተደረጉና ሌሎችም ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

ይህ አካሄድ ክስተቱን እንደ ሽፋን በመጠቀም ከውስጥና ከውጭ ተቀናጅተው ሀገራችንን ለማፍረስለሚሰሩ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በር እየከፈተ መሆኑን መላው የሀገራችን ሕዝብና የዕምነቱ ተከታዮች ግንዛቤ ሊወስዱ እንደሚገባ የጋራ ግብረ-ኃይሉ አመልክቷል።
183 views19:07
Buka / Bagaimana
2023-02-07 10:01:08
177 views07:01
Buka / Bagaimana
2023-02-06 17:50:01
ይሄ ሁሉ ገዳይ ለተዋህዶ ልጆች!!
186 views14:50
Buka / Bagaimana
2023-01-25 09:30:38 ሰበር ዜና
**

"መንግሥት ቤተ
ክርስቲያንና አባቶችን የመጠበቅ ኃላፊነቱን ካልተወጣ ልጆቻቸው ለመጠበቅ ተዘጋጅተናል፤ በቂ ዝግጅትም አድርገናል።"
የመንፈሳዊ ማኅበራትና የኅብረቶች የጋራ መግለጫ
ዛሬ ጥር 16 ምሽት ማኅበረ ቅዱሳን፣ አገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት፣ ምእመናን ኅብረት ፣ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት፣ የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት በጋራ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫውም የማኅበራቱ ተወካዮች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካጋጠማት ታሪካዊ ክስተት አንጻር  ከመቼውም ጊዜ በላይ የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ልዕልና የምናስጠብቅበት እና ከአባቶቻችን ጎን የምንቆምበት ወቅት በመሆኑ በኅብረት መክረን አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል ብለዋል።
ማኅበረ ቅዱሳንን ወክለው የተገኙት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ሥዩም በመግለጫው እንደተናገሩት የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ያቃለለ የነገ የሐዋርያዊ አገልግሎትን ያሰናከለ በመሆኑ አባቶቻችን ይህንን ያማከለ ውስኔ እንዲወስኑ እንጠይቃለን ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም መንግሥት እጁን ከዚህ ሂደት እንዲያነሳ ይልቁንም የእሱ ግዴታ የሆነውን ጥበቃ እንዳያነሳ ይህ ካልሆነ ግን ኦርቶዶክሳውያን ቤተ ክርስቲያን እስከሰማእትነት ለመታደግ የታመኑ ናቸው ብለዋል። ምእመናንም ሳይደናገጡ በጸሎት እንዲተጉ እና ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖራቸውም ጥሪ አስተላልፈዋል።
ከመንግሥት ጋርም በቀጣይ ችግሩን እንዲረዳና ቤተ ክርስቲያን የራሷን ችግር በራሷ እንድትፈታ እድል እንዲሰጣት መወያየታቸውን በመግለጽ የዜጎችን ደህንነት ካልጠበቀ ግን ከተጠያቂነት አይድንም ሲሉ ገልጸዋል።
አንድ ያደረገን ድርጊቱ ሕገ ወጥ መሆኑና ሀገርና ቤተ ክርስቲያን የሚንድ በመሆኑ ነው ያሉት ደግሞ አገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት ተወካይ አቶ ያሬድ ዮናስ ናቸው። ችግሩን ከማወገዝ ባለፈ ከእኛ የሚጠበቀውን ለማድረግ ተዘጋጅተናል፤በእያንዳንዳችን መዋቅርም ስራዎችን ለመስራትም ተነጋግረናል ብለዋል።

የምእመናን ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ኤልሳቤጥ አምዴ በበኩላቸው ውይይት በአንድ ሃሳብና ልብ መከናወኑን ገልጸው ቅዱስ ሲኖዶስ ተደፍሯል፣አባቶች ተደፍረዋል፤ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ካለችበት ችግር ለማውጣት ሁላችንም በቁርጠኝነት ተነሥተናል ብለዋል። በውይይታቸውም በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንደማይደራደሩ አፅንዖት መስጠታቸውን ተናግረዋል።
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና በአባቶች ላይ የተቃጣውን ለመመለስ በአባቶቻችን ጥሪና መመሪያ ተመስርተን ለመሄድ ቃል ገብተናል ያሉት ደግሞ የጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት ተወካይ አቶ አያልነህ ተሾመ ናቸው። አክለውም ይህ የህልውና ጉዳይ ሀገር የማፍረስ ጉዳይ በመሆኑም ዝግጅት አድርገናል ብለዋል።
የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት ተወካይ ወ/ት ፌቨን ዘሪሁን በበኩላቸው ዛሬ በነበረን ውይይት ሁላችንም ከቤተ ክርስቲያን ጎን እንድንሆንና የድርሻችንን ለመወጣት መስማማታቸውን በመግለጽ ለዚህም የአባቶችን መመሪያ እየጠበቁ እንደሆነ ገልጸዋል።
የቅድስት ቤተ ክርስትያንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተገኝተው ለማስረዳት ዝግጅት መጨረሳቸውንም በመግለጫቸው ገልጸዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መንግሥት ከለላውን አንሥቷል ሲሉ ዛሬ ምሽት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
270 views06:30
Buka / Bagaimana
2023-01-25 09:30:28
221 views06:30
Buka / Bagaimana
2023-01-24 13:32:23 ይድረስ ለአባ ሳዊሮስ !!

" አባ ሳዊሮስ " እርስዎን አይደለም መናገር ይቅርና፤ ቀና ብሎ ማየት እንኳን አይገባም ነበር ። ነገር ግን ራስዎትን ፓትሪያርክ ብለው ከመሾምዎት ባለፈ ፣ ሌሎች ኢጲስ ቆጶሳትን በየቦታው በመመደብ የታሪክ ተወቃሽ የሚያደርግ ስህተት ፈፅመዋል። ፈጣሪንም አስቀይመዋል ። አብረዋቸው የበሉ የጠጡትን ሊቃነ ጳጳሳት ወንድሞችዎን ክደዋቸዋል። ለሰይጣን በር ከፍተዋል። እንደው ግን አባ ይህንን ድፍረት ከየት አገኙት ?

አንዳንዶች ከአለቆቻቸው ጋር ቀድመው ያቀዱትን እና የተወያዩበትን በትንቢት አሳበው " ማህበሩን ለሁለት እከፍለዋለሁ ብሎኛል " እያሉ እንዲዘባበቱብን በር ከፍተውላቸዋል። አባ ግልፁን ልንገረዎት መንግስት ይመጣል ይሄዳል ። ዛሬ በአይዞህ ባይ ሊተማመኑ ይችሉ ይሆናል ። ይህ ህዝብ ከተነሳ ግን እኔን አያርገኝ ። እንኳን ለእርስዎ ይቅርና ለመንግስትም ለራሱ ከባድ ነው ። ዋ አለ አሞራ !!

ህዝብ እንዴት እንዳዘነበዎት በየአካባቢው ቃኘት አድርገው ለመረዳት ይሞክሩ ። እውነቱን ልንገረዎት ከመንፈሳዊ ህይወትዎ ይልቅ ለስጋዎ አድልተዋል ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፈተና ይበዛባት ይሆናል እንጂ ማንም ከከፍታዋ አያወርዳትም ፤ እንኳን ለዚች ሚጢጢዬ ሴራ እና ተንኮል ይቅርና ለየትኛውም መጥፎ ተግባር ሸብረክ ብላ አታውቅም ።
፤ ማንም አይነቀንቃትም ።

አባ እርስዎ ለእኛ ለልጆችዎ አርአያ መሆን ሲገባዎት እንደዚህ አይነት የዘር እርኩስ መንፈስ ውስጥ ገብተው በማየቴ እንደ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ከልቤ አዝናለሁ ። በፖለቲካ ድር ውስጥ ተተብትበው የማይወጡት አዘቅት ውስጥ በመግባትዎትም አፍሬበዎታለሁ ። የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ያደረበት ከዘር እና ፖለቲካ መራቅ ነበረበት ። ከዚህ በኋላ ባለፉ ባገደሙ ቁጥር ምን እንደሚባሉ ያውቃሉ " ይሄ እኮ ነው ራሱን ፓትሪያርክ አድርጎ የሾመው " እየተባሉ መሳቂያ መሳለቂያ እንደሚሆኑ አልጠራጠርም። ክብረዎት ብቻ ሳይሆን ግርማ ሞገስዎት ሁሉ ነው የሚገፈፈው ። አባቴ ልቦና ይስጠዎት !!

ኦርቶዶክሳውያን ሆይ ፤ በርካታ የሌሎች እምነት ተከታዬች ድርጊቱን ቢያወግዙም ነገር ግን አንዳንድ የሌሎች እምነት ተከታዮች ሆን ብለው ሊያበሳጯችሁ ብዙ ነገር ሊሉ ይችላሉ ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፀያፍ ቃላትን አላስተማረችንም ። የእኛ እምነት ያስተማረችን ትዕግስትን ፣ የተቸገሩ መርዳትን ፣ ሰውን ማክበርን ነው። ስለዚህ እናንተን ሆን ብለው የሚያነሳሷችሁን መልስ አትስጧቸው። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከዘር በላይ ናት ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከፖለቲካ አመለካከት በላይ ናት ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖታችን ዋነኛ የነፍሳችን ማህተም ናት።

አንድ ሲኖዶስ....የኢት. ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ
አንድ መንበር ... መንበረ ተክለ ሀይማኖት
አንድ ፓትሪያርክ ....ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ !!


ሀሳብ አስተያየት ፡ ጥያቄ ካላችሁ በዚህ @ZeEthiopia_bot በኩል
እኛን ማናገር ትችላላችሁ።


@AntiILLUMINATI666

@AntiILLUMINATI666Discussion
240 viewsedited  10:32
Buka / Bagaimana
2023-01-24 13:32:12
190 views10:32
Buka / Bagaimana