Get Mystery Box with random crypto!

ስፔን ለፍልስጤም ሀገርነት እውቅና ልትሰጥ ነው! ስፔን ለፍልስጤም ነጻ ሀገርነት እውቅና ለመስጠት | Addis መረጃ™

ስፔን ለፍልስጤም ሀገርነት እውቅና ልትሰጥ ነው!

ስፔን ለፍልስጤም ነጻ ሀገርነት እውቅና ለመስጠት መዘጋጀቷን አስታወቀች።ማድሪድ እውቅናውን የምትሰጠው በመጪው ሀምሌ ወር መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ገልጸዋል።

የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸውን በዮርዳኖስ የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በኳታር እና ሳኡዲ አረቢያ በሚኖራቸው ቆይታ በጋዛው ጦርነት ዙሪያ ይመክራሉ መባሉን የስፔን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ከ27ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ ለፍልስጤም ነጻ ሀገርነት እውቅና የሰጡት ዘጠኙ ብቻ ናቸው።የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በአማን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለምልልስ፥ በርካታ የህብረቱ አባል ሀገራት ለፍልስጤም እውቅና እንዲሰጡ ግፊት እየተደረገ ነው ብለዋል።

አየርላንድ፣ ማልታ እና ስሎቫኒያም እስራኤል በሃይል የያዘችው ዌስትባንክ እና የጋዛ ሰርጥ የፍልስጤም ሉአላዊ ግዛት መሆኑን በመቀበል እውቅና ለመስጠት መስማማታቸውን ሳንቼዝ ይፋ አድርገዋል።

እስራኤል የአራቱ ሀገራት ለፍልስጤም እውቅና የመስጠት እቅድ “ለሽብርተኝነት የሚቀርብ ሽልማት” አድርጋ እንደምትመለከተውና የጋዛውን ጦርነት በንግግር ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት የሚያውክ ነው በሚል ተቃውሞዋን ማሰማቷን ሬውተርስ ዘግቧል።

Via Alain
@Addis_Mereja