Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል የዜጎች ግድያና አፈና እንደቀጠለ ነው በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ | Addis መረጃ™

በኦሮሚያ ክልል የዜጎች ግድያና አፈና እንደቀጠለ ነው

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ አደኣ በርጋ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት የኢንጪኒ ከተማ ባለሥልጣንና የጸጥታ አስከባሪዎችን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እንዲገለፅ ያልፈለጉ ነዋሪ ፦ የሰባት ሰዎች አስከሬን ዛሬ ጠዋት ተገኝቷል። ማረሚያ ቤት ተሰብሮ እስረኞች ተለቀዋል፣ ህዳር 28 ቀን ለ29 ቀን 2016 ዓ.ም. አጥቢያ ከሌሊቱ ስድስት ሰኣት ጀምሮ ነው ጥቃት የተፈፀመው፣ የወረዳው ማረሚያ ቤት ተሰብሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ተለቀዋል ብለዋል።

በታጣቂዎቹ ጥቃት የከተማዋ አስተዳዳሪን (ብርሃኑ ሃብትዬ) ጨምሮ የሰዎች ህይወት አልፏል። በተለያዩ ጥበቃ ስራ የሚሰሩ እንዲሁም በማረሚያ ቤት ጥበቃ ላይ ነበሩ የተባሉ ፖሊሶችም መገደላቸውን ሰምተናል፣ ዛሬ ጠዋት ህዝቡ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ወጥቶ አስክረ ሲሰበሰብ ነበር። ቢያንስ ወደ ሰባት አስከሬን ተገኝተዋል፡፡ የተጎዱትም ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

ሌላኛው ነዋሪ ፦ በወረዳው የፖሊስ ጣቢያ ላይም ጥቃት ደርሷል። የወረዳው መሳሪያ ግምጃ ቤትም ተሰብሯል መባሉን ጠዋት ሰምተናል፡፡ ሲንቄ ባንክ ላይም ከፍተኛ የመሰባበር ጉዳት ደርሷል፡፡ ሌሎች ባንኮች ግን ምንም አልሆኑም፡፡ ታጣቂዎቹ በያቅጣጫው ወደ ከተማው መግባታቸው ነው የተሰማው፡፡ እኛ ወጥተን ማየት ፈጽሞ የማይታሰብ ብሆንም ጠዋት እንደሰማነው ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

ሌላኛዋ ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ፣ አሁን ከቤት ለመውጣትም ሰግተናል፡፡ ወንድ ወንዱ ብቻ እየወጣ የሞቱትን ማንሳት ለቅሶ መድረስ ነው ያለው፡፡ ከተማዋ ጸጥ ብላለች፡፡ ሱቆችን ጨምሮ ምንም የተከፈተ ነገርም የለም።(ዶቼቬለ)

@Addis_Mereja